የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጀመረ

Date:

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምዝገባቸውን ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ያሳሰበው አገልግሎቱ፣ ለምዝገባው ሂደት አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችንም ይፋ አድርጓል።

በመመሪያው መሠረት መደበኛ ተፈታኞች በትምህርት ቤቶቻቸው አማካኝነት ምዝገባቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ተፈትነው ውጤት ለማሻሻል ወይም በግላቸው ድጋሚ ለመፈተን የሚፈልጉ ተማሪዎች ደግሞ በራስ-አገዝ (Self-service) የኦንላይን ዘዴ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

የግል ተፈታኞች ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን https://register.eaes.et የተሰኘ ድረ-ገጽ በመጠቀም ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።

ማንኛውም ተፈታኝ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልተመዘገበ በስተቀር ለፈተና መቀመጥ የማይችል መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በጥብቅ አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...