የ22 ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አፈፃፀምና አስተዳደር ምን ይመስላል? የሚል ጥናት ይፋ ሆኗል

Date:

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ2001 እስከ 2023 ባለው 22 ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አፈፃፀምና አስተዳደር ምን ይመስላል? የሚል ጥናት አድርጓል፡፡

በ22 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርት #GDP እና ጠቅላላ ምርቱ ለዜጎች የነብስ ወከፍ ሲሰላ ከ2016 ጀምሮ እየቀነሰ መምጣቱን ጥናቱ አሳይቷል፡፡

የዋጋ ግሽበት በእነዚህ ዓመታት ጨምሯል በዚህም ምክንያት የሃገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚው ሚዛኑን እንዳይጠብቅ አድርጎታል የዜጎች ገቢ እንዲቀንስ አድርጓል ኢንቨስትመንት መቀነሱን ጥናቱ ያሳያል ፡፡

እስከ 2019 ድረስ ባለው ዓመት የማምረት አቅም እያደገ የነበረ ሲሆን ከዛ በኋላ ግን የኢትዮጵያ የማምረት አቅም ባለበት እየሄደ መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡

ባለፉት 2 አስርት ዓመታት ውስጥ የግብርናው ዘርፍ ያገኘው ብድር 7.8 ከመቶ ብቻ ሲሆን ይህም የፋይናንስ  ዘርፍ ድጋፉ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ያሳያል ሲል ጥናቱ ጠቅሷል፡፡

በሀገሪቱ የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ ችግር አለ ከ2020 እስከ 2022 ድረስ ባለው መረጃ መሰረት ከ21 ከመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን የምግብ ዋስትና ችግር ጥያቄ አለባቸው በተለይ በገጠራማ የሀገሪቱ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች የችግሩ ገፈት ቀማስ ናቸው ብለዋል ጥናቱ፡፡

አምራች ተቋማት ወይም ኢንዱስትሪው ለሃገራዊ እድገትና ለስራ ፈጠራ ያለው አበርክቶ እንደ አለማችን ትልቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ገና አላደገም ሲል ጥናቱ ያስረዳል፡፡

በ2023 ኢትዮጵያ ውስጥ ዘርፍ ለጠቅላላ ምርት ያበረከተው አስተዋፅኦ 4.48 ከመቶ ብቻ ነው ይህም ከአለም አቀፉ መመዘኛ ጋር ሲታይ እጅግ ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡

በስራ ፈጠራው ዘርፍ ሲታይ የአምራች ተቋማት አስተዋፅኦው ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡

በ2023 ባለው መረጃ መሰረት ኢንዱስትሪው የፈጠረው የስራ እድል ከአጠቃላይ ጋር ሲወዳደር 6.47 ከመቶ ብቻ ነው አዳዲስ ስራ መፍጠር ላይ ድክመት ይታይበታል ሲል ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ ከውጪ በሚገባ ምርት ለይ የተመሰረተ አምራች ተቋም ነው ያላት ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ተስፋ እየሰጡ ነው ተብሏል፡፡

የጥሬ እቃ እጥረት የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት፣ ውሃ በሚፈለገው ልክ አለማቅረብ አምራች ተቋማት እየገጠማቸው ያለው ፈተና ነው ሲል ጥናቱ አሳይቷል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የፋይናንስ ሴክተር አሁንም አላደገም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ደግፎ በማሸጋገርና የግሉን ዘርፍ በመደገፍ ደረጃ ያለው አቅምም ያነሰ ነው ይላል የኢትዮጵያን ኢኮኖሚክስ ማህበር ይፋ ያደረገው ጥናት፡፡

ለግብርናው ዘርፍ እና ለሌሎችም አምራች ተቋማት ከፋይናንስ ዘርፍ የሚሰጠው ብድር ዝቅተኛ ነው የሚለው ጥናቱ ነገር ግን በሌሎች አማራጮች በተለይ ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ከመደበኛ ውጭ ባሉ የብድር አሰጣጦች ተቋማቱ የሚገኙ ብድር ደግሞ እየጨመረ ነው ይላል ጥናቱ፡፡

የፋይናንስ ዘርፍ አካታችነት እያደገ ቢሆንም የፆታ የገጠርና ከተማ አካባቢዎች አካታችነት ጋር በተያያዘ አሁንም ክፍተቶች አሉበት ተብሏል፡፡

ከ2002 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ከቀረጥ የሚሰበሰበው ገቢ በአመት በ2 መቶ በመቶ ማደጉን ጥናቱ ጠቅሷል፡፡

ይሁንና የማይወርድ የዋጋ ግሽበት የነበረ በመሆኑ የሰዎች የመግዛት አቅምን አዳክሟል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከፍተኛ የብድር ጫና እያለባት ከወጪ ንግድ የምታስገባውና ከቀረጥ የምትሰበስበው ገቢ ያነሰ መሆኑን በከፍተኛ ርብርብ የወጪ ንግዷን ማሳደግ እንዳለባት ከቀረጥ የሚሰበሰበው ገቢ ለማሳደግ መስራት እንዳለባት ጠቋሚ ነው ብሏል ጥናቱ፡፡

ሸገር ጥናቱን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ኢትዮጵያ የድህነት ምጣኔው በ2018/19 ከነበረበት 30 ከመቶ ወደ 26 ከመቶ ዝቅ ቢልም ከ2015/16 ከነበረበት 24 ከመቶ ጋር ሲነፃፀር ከፍ ብሏል ይላል የተደረገው ፡፡

ይህም ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ የደህንነት ምጣኔ 26 በመቶ እንዲደረሰ ያሳያል፡፡

በጥናቱ ወቅት በድህነት ላይ የሚኖሩ ቤተሰቦች ፍጆታቸው ገቢያቸው በመቀነሱ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት ምርቶች እንዲቀንሱ፣ የዋጋ ግሽበት እንዲጨምርና ድህነት በሀገሪቱ ከፍ እንዲል አድርጓል ተብሏል፡፡

የዋጋ ግሽበቱና የማክሮ ኢኮኖሚው አለመረጋጋት በሀገሪቱ ከድህነት በታች የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል፡፡

ከ2020 ጀምሮ የሰዎች መተማመን በመቀነሱ የነገሮች ተገማች አለመሆን መጨመሩ አስተዳደራዊ መዳከም ሃገሪቱ ውስጥ እንዲንሰራፋ አድርጓል ሲል ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

የእርስ በእርስ ጦርነቱ ኦኮኖሚው እንዲቀዛቀዝ የውጪ ባለሃብቶች ወደ ኢንቨስትመን መሳብ እንዲዳከም ማድረጉን ጥናቱ አሳይቷል፡፡

ከ2001 እስከ 2023 የ22 ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተመለከተ ተቋሙ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡ 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...