የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሦስተኛ ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት 38ኛ ዓመት የዕረፍታቸው መታሰቢያ በወላይታ ሀገረ ስብከት በሶዶ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመመሪያው ሓላፊዎች ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድባብ መከበሩን የሀገሩ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቦክቻ ኤንጋ ለሚዲያችን አሳውቀዋል።
መልአከ ሰላም እንዳሉት የቅዱስነታቸው መታሰቢያ ላለፉት ዓመታት ሻማ በማብራት ብቻ ሲታሰብ ቢውልም የሀገረ ስብከቱ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ አባቶች ካህናት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በመወያየት ክብረ በዓሉ በደመቀ ሁኔታ በማኅሌት፣ በቅዳሴ ተከብሮ እንዲውል በወሰንነው መሠረት ተከብሯል ብለዋል።
አክለውም ቅዱስነታቸው ግንቦት 12 ቀን 1980 ዓ.ም. በሕመም ላይም ሆነው ብዙ በደከሙበት ቦታቸው መጥተው ከሕመማቸውጋ እየታገሉ የመሠረት ድንጋይ ጥለው ሕመሙ ሲበረታባቸው ወደ አዲስ አበባ አቅንተው ግንቦት 28/1980 ዓ.ም ቢያርፉም በሀገረ ስብከቱ ለበርካታ ዓመታት ዕረፍታቸው ሲታወስ መቆየቱንና አሁን ግን ብፁዕ አባታችን በተገኙበት መልኩ በደማቅ ሁኔታ መከበሩን ገልጸዋል።
. ተ.ሚ.ማ. አዲስ አበባ]
