የተመድ 2026 መደበኛ በጀት 3.45 ቢሊየን ዶላር አፅድቋል

Date:

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ለተቋሙ የ2026 የ3.45 ቢሊየን ዶላር የመደበኛ በጀት አፅድቋል።

ሰላምና ደህንነት፣ ዘላቂነት ያለው ልማትና የሰብዓዊ መብት የተቋሙ ሶስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች ሲሆኑ እነዚህን ስራዎች ለመሸፈንም 193 ሃገራት ያሉበት ጠቅላላ ጉባኤ የ3.45 ቢሊየን ዶላር በጀት ለ2026 አፅድቋል።

የፀደቀው በጀት የተመድ ዋና ፀሃፊ ካቀረቡት እቅድ በ200 ሚሊየን ዶላር የበለጠ ነው ሲባል ለ2025 ከፀደቀው  የ3.72 ቢሊየን ዶላር በጀት በ7% ያነሰ ነው።

የተመድ መደበኛው በጀት የተመድን የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ፍትህና ህግ፣ ሰብዓዊ መብት፣ ቀጣናዊ ትብብርና የህዝብ ግንኙነትን በተመለከተ ለሚሰሩ ስራዎች ሲውል ከተመድ የሰላም ማስከበር ከሚያዘው በጀት የተለየ ነው።

የተመድ የሰላም ማስከበር የበጀት አመት ከፈረንጆቹ ሃምሌ ወር እስከ ሰኔ ሲቆይ መደበኛው በጀት ግን ከጥር እስከ ታህሳስ ወር ይቆያል።

ለተመድ የሰላም ማስከበር የሚውለው የ2025/26  በጀትም ከባለፈው አመት ቅናሽ አሳይቶ 5.38 ቢሊየን ዶላር ሆኖ መፅደቁ ይታወሳል።

ተመድ ከበጀት ጋር በተያያዘም ነገ ከሚጀምረው አዲስ አመት ጀምሮ ከ2900 በላይ የስራ ቦታዎች ይጠፋሉ ብሏል።

ተመድ በተደጋጋሚ ሃገራት መክፈል የሚጠበቅባቸውን ክፍያ አለመፈፀማቸው የበጀት ችግር እየፈጠረበት እንደሆነ ሲናገር መቆየቱ የሚታወስ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአንጋፋውን ጋዜጠኛ ድምጽ እንደገና እንስማ

ኑ ጥቂት ድጋፍ አድርገን ተስፋ እናለምልም ‼️ ባለ ወርቃማ ድምጹ...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...