የተመድ ዋና ጸሐፊ ኢራን እና አሜሪካ “በቅን ልቦና” ወደ ድርድሩ እንዲገቡ ጠየቁ

Date:

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ እና ኢራን ሊያደርጉ ያቀዱትን የሰላም ንግግር በበጎ እንደሚቀበሉ ገልጸው፤ ሁለቱም ወገኖች “በቅን ልቦና” ወደ ድርድር እንዲገቡ አሳሰቡ።

በመንግሥታቱ ድርጅት የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ንግግር ያደረጉት የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ስቴፋን ደዣሬክ፤ ጉቴሬዝ “ሁሉም ወገኖች ይህንን የዲፕሎማሲ እድል በመያዝ ወደ ዘላቂ እና አጠቃላይ ስምምነት ለመድረስ በቅን ልቦና እንዲሳተፉ” መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊው፤ ንግግሩ ውጥረቱን “የማርገብ እና ወደ ግጭት እንዳይመለስ የመከላከል” እድል እንደሚሰጥም አስታውሰዋል።

“ዋና ጸሐፊው፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት ከሰላማዊ አማራጭ ውጪ ዓለም አቀፍ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችል ተጨባጭ አማራጭ እንደሌለ አጽንኦት ሰጥተዋል” ሲሉ ቃል አቀባዩ ደዣሬክ ተናግረዋል።

የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የግል ልዑክ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ለማገዝ ቀጣናው ውስጥ እንደሚገኙም ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...