‘የትዝታዬ ማሕደር’ የደራሲ ጌታቸው መፅሐፍ ተመረቀ

Date:

” ዳግላስ ጴጥሮስ “በሚለው የብዕር ስሙ የሚታወቀው፣ በርካታ መፅሀፎችን እና መጣጥፎችን ያስነበበው ደራሲ ጌታቸው በለጠ ‘የትዝታዬ ማሕደር’ በሚል ርዕስ የሕይወት ታሪኩን ፅፎ ዛሬ ሚያዝያ 5 ቀን 2017 በባህል ሚኒስቴር አዱሱ ሕንጻ (ወመዘክር)
ተመረቀ!

ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ የደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገለ ሲሆን በየጊዜው በሚሰጣቸው የማህበራዊ እና የኪነ ጥበባት ሂሶችም ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ ቃለ- መጠይቆች በመስጠት ከበሬታን ያገኘ ደራሲ ነው።

ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በጋዜጦች ላይ በመፃፍ አቅሙን ያሳየ የብዕር ሰው ነው።ደራሲ ጌታቸው በለጠ/የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዚደንት ሆነዉ ያገለገሉና በርካታ መጽሃፍቶችን ማዘጋጀት የቻለ የስነፅሁፍ ባለሙያ ነዉ።

ደራሲ ጌታቸው በለጠ ያስመርቀው መፅሀፍ፣448 ገፆች ያሉት ሲሆን ከልጅነት እስከ አዋቂነት ዕድሜ ያሳለፈውን ሕይወት በመፅሀፉ ላይ አካቷል፡፡

የደራሲ ጌታቸው መፅሀፍ 1000ብር የሚሸጥ ሲሆን በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ ታዋቂ ደራሲያን፣ እና የቅርብ ወዳጆቹ ንግግር አድርገዋል ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...