በዝውውር መስኮቱ ሰባት ተጨዋቾች ያስፈረሙት መድፈኞቹ አሁንም ሌላ ተጨዋች በመመልከት ላይ ናቸው።
መድፈኞቹ ተከላካዩ ፔሮ ሂንካፔን ከባየር ሌቨርኩዝን ለማስፈረም በንግግር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።
በሌላ በኩል አርሰናል ጃኩብ ኪውዮርን ለፖርቶ ለመሸጥ ድርድር ላይ ሲሆን ሚኬል አርቴታ ፔሮ ሂንካፔን ተተኪ ማድረግ ይፈልጋሉ።
ተጨዋቹ በቀድሞው ጊዜ በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ስር በግራ መሐል ተከላካይ እና ተመላላሽ ሆኖ ሲጫወት ተስተውሏል።
በተጨማሪም በአሰልጣኙ የአጨዋወት ዘይቤ የክንፍ ተመላላሽ ተጨዋች ሆኖ ተጫውቷል።
አርሰናል በቀጣይ ፖርቶን ለመቀላቀል ንግግር ላይ ያለውን ኪውዬር ጨምሮ ሎኮንጋ ፣ ዚንቼንኮ ፣ ፋብዮ ቬራ እና ሬስ ኔልሰንን ለመሸጥ እየሰሩ ነው።
መድፈኞቹ በተጨማሪም የመጨረሻውን የዝውውር ሳምንት የአካዳሚ ተጨዋቾችን ለመሸጥ እና በውሰት ለመስጠት ለመጠቀም ማሰባቸው ተገልጿል።
@Tikvahethsport
