አውስትራሊያ የዩክሬንን ጦር ማሰልጠኗን ቀጥላለች ተባለ።ከዚህ ቀደም አውስትራሊያ ወደ አውሮፓ የተለያዩ አካባቢዎች ባለሙያዎችን በማሰማራት ኪዬቭን ስታግዛት እንደነበር ተወስቷል።
ዩናይትድ ኪንግደም ላይ መሰረቱን ባደረገ ዘመቻ በመሳተፍም አውስትራሊያ ለዩክሬን ጦር ስልጠና መስጠቷ አይዘነጋም።
አሁን ላይ ግን ወደ ዩክሬን ድንበር ዘልቆ የማሰልጠን ውጥን ተይዟል።
ይህ ደግሞ ካንቤራ ኪዬቭን ለማገዝ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል።
በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ ፖላንድ የአውስትራሊያ ባለሙያዎች ያመራሉ።
ሩሲያ እና አውስትራሊያ ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉም ማሳያ ሆኗል።
መሰረታዊ ስልቶችን አዲስ ተመልምለው ለመጡ ወታደሮች በስልጠና መልክ እናሳያለንም ብላለች አገሪቱ።
የአመራርና ወታደራዊ ክህሎቶችን እንዴት ማዳበር እንደሚቻል ለዩክሬናውያን ስልጠና እንሰጣለንም ብለዋል መከላከያ ሚኒስትሩ ሪቻርድ ማርለስ።
ከ2023 ጀምሮ አውስትራሊያ በተለያዩ የስልጠና ሂደቶች ዩክሬናውያንን ስትደግፍ እንደነበርም መረጃው ይጠቁማል።
መከላከያ ሚኒስትሩም የወሰደውን ጊዜ ቢወስድም የዩክሬንን ምልምል ወታደሮች ማሰልጠናችንን እንቀጥላለን ብለዋል ።
ሞስኮ አደገኛ አፀፋ ሊኖራት ይችላል የሚል ስጋትም ተደቅኗል።
ዘገባው የዘ አውስትራሊያን ጋዜጣ
