የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

Date:


የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።

በዚህም የቤኒን፣ ቦትስዋና፣ ኮትዲቯር፣ ናሚቢያ እና ዚምባቡዌ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጉባኤው አስቀድሞ የካቲት 4 እና 5 ቀን የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 48ኛው መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል።

ጉባኤው “የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና አስተማማኝ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...