የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አዲሱን አርማውን ይፋ አደረገ

Date:

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አዲሱን አርማውን ይፋ አደረገ

👉 ድርጅቱ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዮ ክብረ በዓሉን ማክበር ጀ

በኢትዮጵያ የመድን ኢንዱስትሪ ቀዳሚ የሆነውና በአዋጅ ቁጥር 68/1968 ዓ.ም የተመሠረተው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት፤ 50ኛ ዓመት የወርቅ አዩቤልዩ የምሥረታ በዓሉን በተለያዩ ኩነቶች ማክበር መጀመሩን አስታውቋል።

የበዓሉ ዝግጅት ከሕዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ሁለት ወራት የድርጅቱን የ50 ዓመት ጉዞውን በሚያሳዩ የተለያዩ መርሐ-ግብሮች እንደሚያከብር ገልጿል።

በዛሬው ዕለትም የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የድርጅቱ የበላይ አመራሮች እንዲሁም የድርጅቱ ሠራተኞች በተገኙበት በዓሉን አስጀምሯል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ታደሰ፤ ተቋሙ ላለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያ ትልቅ ሚናን የተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተቋቋመ 1968 ዓ.ም ጀምሮ ለ19 ዓመታት ብቸኛው የመድን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሆኖ መቆየቱን አንስተዋል።

የድርጅቱ አጠቃላይ ሀብት መጠን 24 ነጥብ 3 ቢሊየን መድረሱን ገልጸው፤ ከሚያገኘው ትርፍ ለመንግሥት ገቢ ማድረግና ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል ብለዋል።

እስከ ጥር መጨረሻ የሚቆየው ክብረ በዓሉ “የደንበኞች ቀን” በሚል መሪ ቃል በጋራ ሲሰሩ የቆዩ ደንበኞችን ምስጋና እና የእውቅና መስጠት መርሃ ግብር እንዲሁም የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በመከወን የሚቀጥል መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከክብረ በዓሉ ጋር ተያይዞ ያለውን ይዘት በጠበቀ መልኩ መለያውን ማሻሻሉን የተገለጸም ሲሆን፤ አዲሱን አርማውን ይፋ አድርጓል።

አዱሱ አርማው የራሱ የሆነ ትርጓሜን የያዘ መሆኑንም ተጠቁሟል።

ሌላው ንግግር ያደረጉት የሠራተኞች ማህበር ሊቀመንበር ደስታ በርሄ፤ ሠራተኞች የተሻለ ሥራ ሰርተው የተሻለ ደሞዝ መክፈልና የኑሮ ጫና መቋቋም እንዲችል የሚያደርግ ጥናት እየተሰራ መሆኑም አንስተዋል።

የሠራተኞች ጥያቄዎች ምላሽና መፍትሔ እየተሰጠ የሚቀጥል መሆኑን አክለዋል።

ድርጅቱ ከወራት በፊት 38ኛውን ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ጉባዔውን ያካሄደ ሲሆን፤ የ2017 በጀት ዓመት 6 ነጥብ 56 ቢሊዮን ብር የካሳ ክፍያ መፈጸሙን መግለጹ አይዘነጋም።

አሐዱ ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...