የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027 አፍሪካ ዋንጭ በ28 ሳይሆን በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
የአህጉሪቱ እግር ኳስ ገዢ ቀደም ሲል የተሳታፊዎቹ ቁጥር ወደ 28 አሳድጎ ውድድሩን እንደሚያካሂድ በተደጋጋሚ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
በቀጣይ አመት የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የምስራቅ አፍሪካዎቹ ሀገራት ኬንያ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ በጣምራ እንደሚያዘጋጁት ይታወቃል።
