ለመጀመርያ ጊዜ ለፖርቹጋል ከ15 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገለት ክርስቲያኖ ጁኒየር የቭላትኮ ማርኮቪች ዋንጫን አሳክቷል።
በቀድሞው የክሮኤሽያ አንጋፋ ተጫዋች አሰልጣኝ እና የፌደሬሽኑ ፕሬዝደንት ቭላትኮ ማርኮቪች ስም በተሰየመው ወድድድር ፖርቹጋል ክሮኤሽያን 3 ለ 2 ባሸነፈችበት ጨዋታ ሁለት ግቦችንም አስቆጥሯል።
ልክ እንደ አባቱ 7 ቁጥር መለያ ለብሶ ሚጫወተው ጁኒየር ለሰባተኛ ጊዜ በተደረገው የመታሰቢያ መድረክ ባሳየው ብቃት ብዙዎችን አስደንቋል።
በተለይም የመጀመርያ ግቡን ካስቆጠረ በኋላ እንደ አባቱ ክርስቲያኖ ሁሉ ደስታውን በተመሳሳይ መንገድ ገጿል።
በልጁ እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆኑን የተናገረው የአል ናስሩ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምንም እንኳን በመካከላቸው የ26 አመት ልዩነት ቢኖርም በአንድ ወቅት ከልጁ ጋር መጫዎት እንደሚፈልግ መናገሩም ይታወሳል።
