የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ሥልጠና አከናወነ

Date:

ኩባንያችን ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመተባበር በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሂደትና በቀጣይ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ያካሄደ ሲሆን፤ በመድረኩ ላይም የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የኮከስ አመራሮችና የጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ራዕይን ዕውን ለማድረግ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን ለአባላቱ ያብራሩ ሲሆን፤ ኩባንያችን ለስትራቴጂው መሳካት በተለይም በመሰረተ ልማት፣ በዲጂታል መድረኮች እንዲሁም በሥነ-ምህዳር ግንባታ ረገድ የነበረውን ቁልፍ አበርክቶ አብራርተዋል።

ኩባንያችን “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ግብን ለማሳካት የሦስት ዓመት ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር መግባቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ሥነ-ምህዳር፣ ቴሌብር፣ በሉዓላዊ ክላውድና በሳይበር ደህንነት የታቀዱ ስትራቴጂካዊ እቅዶች ተብራርተዋል።

የምክር ቤት አባላቱ በውይይቱ ወቅት ለዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ያላቸውን የላቀ አክብሮትና አድናቆት የገለጹ ሲሆን፤ በተለይም ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ተቋሙን በራዕይ፣ በእውቀትና በቁርጠኝነት እየመሩ የሚገኙ ስትራቴጂካዊ መሪ መሆናቸውን በመጥቀስ ልባዊ እውቅና ሰጥተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እንደ ስማቸው ሁሉ “ፍሬያማ” መሆን የቻሉ መሪ መሆናቸውንና ለዚህም በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ተምሳሌት መሆናቸውን አጽንኦት በመስጠት፤ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የሚኖሩ ጠንካራ መሪ መሆናቸውን በኩራት ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣምና ተቋሙን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር ረገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ያሳዩት ብቃትና የአመራር ጥበብ ትልቅ ክብርና አድናቆት ከአባላቱ ቀርቧል።

ኩባንያችን አርአያነት ያለው መሆኑን የገለጹት የምክር ቤት አባላቱ፤ ተቋሙ “የሀገር ኩራት” ከመሆኑም ባለፈ “የኢኮኖሚው ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሞተር” መሆኑን በአጽንኦት መስክረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን የቀረቡት አድናቆቶች ለቀጣይ የሥራ ትጋት ትልቅ ኃላፊነትና አደራ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ይህም ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን መሳካት በላቀ ቁርጠኝነት ለመስራት እንደሚያነሳሳ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም መድረኩ ፍሬያማ፣ ስኬታማና አስተማሪ እንደነበረ የገለጹት የምክር ቤቱ አባላት፤ ኩባንያችን የሀገሪቱን ዲጂታል ሽግግር ይበልጥ ለማፋጠን እንዲችል የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...