የጦርነት ዘገባ ጋዜጠኞች ተሸለሙ

Date:

የፈረንሳዩዋ የባዩ ከተማ የምታስተናግደው የጋዜጠኞች የጦርነት ዘጋቢ የሽልማት ስነ ስርዓት ለ32ኛ ጊዜ የጠካሄደ ሲሆን፤ ፍልስጤማዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሳሄር አልግሆራ፣ የባዩ የጦርነት ዘጋቢ ሽልማትን አሸንፏል፡፡

ትናንት ቅዳሜ በተካሄደው በዚሁ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ለዙማ ፕሬስ የሚዘግበው ፍልስጥኤማዊ የፎቶ ጋዜጠኛ ሳሄር አልግሆራ ለራሱ የመጀመሪያው የሆነውን ሽልማት አሸንፏል፡፡

ጋዜጠኛው ለሁለት ዓመት ገደማ በጋዛ ሰርጥ በሃማስና እስራኤል መካከል ሲካሄድ የቆየውን አውዳሚ ጦርነትና የደረሰውን አስከፊ ሰብአዊ ቀውስ «በእሳት እና ረሃም መካከል » በተሰኘውና በተከታታይ በሰራቸው የፎቶ ዘገባዎቹ ነው ለሽልማት የበቃው፡፡

ከሳሄር በተጨማሪ የጀርመኑ የሳይት ጋዜጣ ዘጋቢ ዎልፍ ጋንግ ባየር፣ በህትመት ጋዜጠኝነት ዘርፍ አሸናፊ መሆኑ ተነግሯል።

ጀርመናዊው ባየርን ለአሸናፊነት ያሳጨው «የተረሳው» በሚል ርዕስ በሱዳን ካርቱም ብቻውን ስለቀረና በከፍተኛ ጫና ውስጥ ብቸኛ የቀዶ ህክምና ስለሚሰጥ አንድ ሆስፒታል የሰራው ዘገባ ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ፤ ለፍራንስ 24 የሚሰሩት ጁልዬ ዱንገልሆፍ ፣ ሶፊያ አማራና ጄምስ አንድሬ በጥምር በቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት መስክ አሸናፊ ሆነዋል።

የፍራንስ 24 ጋዜጠኞችን ጨምሮ ሁሉም ዘጋቢዎች በዩክሬን ፣ ጋዛና ሱዳን ጦርነቶች ውስጥ በተለያዩ የዘገባ መስኮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የዘገባ ስራቸውን ሲያከናዉኑ የነበሩ መሆናቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተሰጠ የኀዘን መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና...

 የ2026 የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓሪስ ውጪ በለንደን በተካሄደው ታላቅ የሽልማት...

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...