“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን ውስጥ ብዙ ትዝታ፣ ብዙ ፍቅር እና የማይረሳ የሕይወት ጉዞ አብረን አሳልፈናል።
የውድ ጓደኛዬን ህልፈት ስሰማ ልቤ በእጅጉ አዝኗል፤ ስሜቴንም በቃላት ለመግለጽ አቅቶኛል። ነገር ግን ሞት ከዚህ ዓለም ወደ ጌታ የሚደረግ ሽግግር መሆኑን እናምናለን።
መሐሪው አምላክ ነፍሱን በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ ያኖርለት፤ በገነትም ዕረፍት ያድርግለት። ለቤተሰቦቹና ለምንወደው ሁሉ የመንፈስ ቅዱስን ማጽናናት ይስጥ።
ነፍሱን ይማር፤ መንግሥተ ሰማያትንም ያውርሰው። አሜን።”
የአብሮ አደግ ህመም
ነፍስ ይማር!
ይሁኔ በላይ
