ጄጄ ግሩፕ የ700 ሚሊዮን ብር የህንፃ ግንባታ አስጀመረ

Date:

በኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ዘርፍ ለዓመታት የቆየው ጄጄ ግሩፕ (JJ Group)፣ በአዲስ አበባ እምብርት ኡራኤል አደባባይ አቅራቢያ ለንግድ እና ለመኖሪያ የሚውል ባለ 12 ፎቅ ዘመናዊ የህንፃ ግንባታ በይፋ ጀምሯል።

ለዚህ ፕሮጀክት ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግም ታውቋል።

የጄጄ ግሩፕ ስራ አስፈጻሚ እና የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጀበል ጀማል ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፤ ይህ አዲስ ፕሮጀክት ባለ 12 ወለል ሲሆን፣ ሁለት የመሬት በታች መኪና ማቆሚያዎችንም ያካተተ ነው።

ህንፃው የንግድ እና የመኖሪያ አገልግሎቶችን አጣምሮ የያዘ (Mixed-use) ሲሆን፣ ከ60 በላይ የንግድ ሱቆችን፣ ለቢሮ የሚሆኑ ሰፊ ቦታዎችን እና 31 ባለ ሁለት መኝታ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በውስጡ ይዟል።

የግንባታው ዲዛይን የመኖሪያ እና የንግድ መግቢያዎችን ለየብቻ በማድረግ የነዋሪዎችን ሰላምና ደህንነት በልዩ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

እንደ ሥራ አስፈጻሚው ገለፃ፣ በህንፃው ላይ የሚገኙ የንግድ ሱቆች በ8 ወራት ውስጥ ተጠናቀው ለባለቤቶቻቸው የሚረከቡ ሲሆን፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶቹ ደግሞ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ ይሆናሉ።

ድርጅቱ የዋጋ ንረትን ስጋት ለመቀነስ ለአስር ቤቶች ብቻ የሚቆይ ልዩ የቅድመ-ሽያጭ ቅናሽ ማዘጋጀቱንም አብስሯል።

አቶ ጀበል አክለውም፣ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት አዲሱ የሪል እስቴት አዋጅ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመው፤ ድርጅታቸው ግንባታውን በተቀመጠለት የጥራት ደረጃና የጊዜ ገደብ ለማስረከብ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በዕለቱ በጀጀ ግሩፕ አማካይነት የግንባታ ሥራ የተሠራላቸው ደንበኞች ምስክርነት የሰጡ ሲሆን የኮንስትራክሽን ድርጅቱ በጊዜ በማስረከብ ልዩ ስም ያተረፈ መሆኑን ምስክርነት ሰጥተዋል።

በተለይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ጀበል ጀማል የግንባታ ኮንስትራክሽን ሳይት ድረስ በማቅናት ለደንበኞች ርካታ የሚለፉ መሆናቸውን በዕለቱ የታደሙ እንግዶች ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሪል ስቴት ማህበር የቦርድ አባልና የጃምቦ ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ደበበ ሰይፉ በዕለቱ የአቶ ጀበል ትጋት የሚደንቅ መሆኑን የመሰከሩ ሲሆን በሪል ስቴት ዘርፉም ትልቅ ሥራ የመስራት አቅም አላቸው ብለዋል።

አቶ ጀበል ጀማል፣ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት ማህበር እንዲመሠረትና አሁን ላለበት የዕድገት ደረጃ እንዲደርስ መጣራቸውን አቶ ደበበ መስክረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር በዓለም የምግብ ምርምር ድርጅት ሹመት ተሰጣቸው

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአግራ (AGRA) የቦርድ ሰብሳቢ...

አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በካናዳ ሀገር ሊሸለሙ ነው

የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በንግዱ...

በምክክሩ ወቅት በሀሳብ ልዩነት “አድማ የመቱ” ነበሩ

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በ22ኛው ቀን ውሎው በስልታዊ ቡድን ደረጃ...

በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለዉ ግጭት እንዳሳሰበው የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን ገለፀ

የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን  በኢትዮጵያ ፌደራላዊ  መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ...