በየዓመቱ የሚዘጋጀው “የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ” ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም በስካይላት ሆቴል ተካሄዷል።
ቅዳሜ አመሻሽ ላይ የተካሄደው”የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ” የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ እንደተጠቀሰው ምስጋና ባህል እንዲያደርግ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው ይህ መሰናዱ ከጠዋት አንስቶ በተለያየ ከተሞች በአዳማ ፣በአዲስ አበባ፣በሐረር፣በሃዋሳ መምህራንን፣የህክማና ባለሙያዎችን፣የመኪና አስሽከርካሪዎች፣የፅዳት ባለሙያዎችን እናመሰግናለን እያለ መቆየቱም ተገልፃል።
በተለያዩ ዘርፎች ህይወት ጣፋጭ እንዲሆን ትልቅ ሚና አበርክታችኋል ያላቸው ሲያመሰግን አምሽቷል።
