ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ አሜሪካውያን እና የአሜሪካ መሪዎች የራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም አላቸው እኛም የነርሱን ፍላጎት እናከብራለን ብለዋል፡፡
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው አንዳቸው የሌላውን ብሄራዊ ጥቅም መከባበርን በተመለከተ ከአሜሪካ ምላሽ እንደምትጠብቅ ተናግረዋል።
ፑቲን ከሩሲያዉ ጋዜጠኛ ፓቬል ዛሩቢን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ አሜሪካውያን የአሜሪካ ህዝቦች እና የአሜሪካ መሪዎች የራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም አላቸው፣ እኛም እናከብራለን ብለዋል።
ይህ አስተያየት የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን እና ከዩክሬን አቻቸው ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ለመነጋገር ባቀዱበት ወቅት ነው።
ትራምፕ በኢስታንቡል በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ከፍተኛ ደረጃ ያለው የሰላም ድርድር አመቻችተዋል፡፡
ሁለቱም ወገኖች እያንዳንዳቸው 1 ሺህ የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ እና የእርቅ ስምምነት ለማድረግ ድርድሩን ለመቀጠል ተስማምተዋል።
