በጥቃቱ ከ20 በላይ ሰዎች ህይወት መቀጠፉንም ካቡል አሳውቃለች።
የአፍጋኒስታን መከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱ ትምህርት ቤቶችን እና መኖሪያዎችን ዒላማ ያደረገ ነው በሚል ከሷል።
የፓኪስታን መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በቅርቡ በግዛታችን ውስጥ ጥቃት እንዲደርስ ከጀርባ አሉበት ያላቸው ሀይሎች ካምፕና መደበቂያ ላይ ጥቃት አድርሻለሁ በሚል አስተባብሏል።
በኢስላማባድ ሺያ መስኪድ ላይ ከደረሰው የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ጀርባ የነበሩ ታጣቂዎችን ዒላማ አድርጊያለሁ የምትለው ፓኪስታን በተደጋጋሚ ወደ አፍጋኒስታን የአየር ክልል ብቅ በማለት አሸባሪዎችን አደብ አስገዛለሁ በሚልም ዝታለች።
ታሊባን መራሹ የአፍጋኒስታን መከላከያ መኖሪያ ቤቶችንና ሀይማኖታዊ ትምህርት ቤቶችን ኢስላማባድ ደብድባለች፤በዚህም በርካቶች ቆስለዋል ፤ህይወታቸውንም አጥተዋል ሲል ወቅሷል።
እስካሁንም ህይዎታቸውን ያጡ ሰዎችን ቁጥር በትክክል ማወቅ እንዳልተቻለም ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በድንበር ግዛቶች አቅራቢያ ናንጋርሃርና ፓክቲካ አካባቢ የደረሰ ጥቃት ነው።
በደቡብ ኤዥያዎቹ ጎረቤት አገራት መካከል ተደርጎ የነበረውን ተኩስ አቁም የሚያፈርስ ድርጊት ሆኗል።
የፓኪስታን የማስታወቂያ ሚኒስቴር በተጠና መልኩና በመረጃ ተደግፈን በሰባት የፓኪስታን ታሊባን (ቲ ቲ ፒ) ካምፖችና መደበቂያዎቻቸው ላይ መከላከያው ጥቃት አድርሷል የሚል መልዕክት በኤክስ ገፁ አስተላልፏል።
የካቡል መከላከያ ኢስላምአባድ ዓለም አቀፍ ህግን ጥሳለች የበጎ ጉርብትናን መርህ ችላ ብላለች በሚል ወቅሷል።
አፀፋዊ ምላሹንም ፓኪስታን ትጠብቅ ብላለች አፍጋኒስታን።
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው።
