ህዝባዊ ተቃውሞ በቦረና!

Date:

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ 14 ወረዳዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ፣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና እና ቦረና ዞኖች ሕዝባዊ ተቃዉሞ መቀስቀሱን ተዘግቧል ፡፡

ይህ ውሳኔ የተወሰነው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤው ላይ መሆኑን ያስረዱት ምንጮች፣ ይህንኑ ተከትሎ በቅርቡ እንደ አዲስ በተዋቀረው የምስራቅ ቦረና ዞን መቀመጫ ነጌሌ ቦረና ከተማና የቦረና ዞን መቀመጫ በሆነችው ያቤሎ ከተማ፣ እንዲሁም በሌሎች ወረዳዎች የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ በምክር ቤቱ የተወሰኑት 14ቱ ወረዳዎች በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሚገኙት ቦረና፣ ባሌ፣ ሐረርጌ እንዲሁም ከድሬደዋ አካባቢዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው እንደሆኑ ምንጮች መናገራቸው ተጠቁሟል፡፡

ዋዜማ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...