ለታሊባን ዕውቅና በመስጠት ፈር ቀዳጇ ሩሲያ

Date:

ሩሲያ ለአፍጋኒስታኑ የታሊባን መንግስት ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ አገር ሆነች፡፡

ሞስኮ ታሊባንን በከፍተኛው ፍርድ ቤቷ ሚያዚያ ላይ ከሽብርተኛ ዝርዝር ማስወጣቷ ይታወሳል፡፡

ውሳኔው ቀጠናዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን ለማሳደግ ለሩሲያ ዕድል ይፈጥርላታል ተብሏል።

ከአራት ዓመታት በፊት የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ሲወጣ ካቡልን የተቆጣጠረው ታሊባን፣ አገሪቱን በመምራት ላይ ይገኛል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ውሳኔው በአፍጋኒስታን እና በሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት እና ትብብር በተለያዩ ዘርፎች ያጠናክረዋል ብሏል።

ሞስኮ በዓለም ላይ ለታሊባን መንግስት ዕውቅና የሰጠች ብቸኛዋ ሀይልም ሆና ተመዝግባለች።

“ይህ የጀግና ውሳኔ ለሌሎችም ምሳሌ ይሆናል” ሲሉ የአፍጋኒስታኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር ክሃን ሙታቂ ሀሳባቸውን በቪዲዮ አጋርተዋል፡፡

ሩሲያ በቀጠናው ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሚናዋን ለማጉላትም እንደመልካም አጋጣሚ ትጠቀምበታለች ተብሏል።

ጉዳዩን አሜሪካ በጥንቃቄ  እንደምታየውም እየተነገረ ነው፡፡

አልጀዚራ እንዳስነበበው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...