ለእስራኤል ሲሰልል አግኝቼዋለሁ ያለችውን ዜጋዋን በሞት ቀጣች

Date:



‎ኢራን ለእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ ሲሰልል ነበር በማለት በቁጥጥር ስር አውላው የነበረውን ዜጋዋን ዛሬ በሞት መቅጣቷን የኢራን መንግሥት የዜና አውታር ኢርና ዘግቧል።

‎ኢስማኢል ፌክሪ፥ አሚር ከተባለ የሞሳድ ወኪልና ከሌላ የእስራኤል ሰላይ ጋር በመገናኘት ምስጢራዊ የሆኑ የኢራን ቦታዎችን የሚመለከትና ሌሎች ቁልፍ መረጃዎችን ለእስራኤሉ የስለላ ድርጅት በማቀበል ተጠርጥሮ በዲሴምበር 2023 በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር።

‎እንደ ኢርና ዘገባ፥ ተጠርጣሪው በኢራን መንግሥት የቀረበበትን ክስ ከማመኑም በተጨማሪ ለዚሁ ሥራው በክሪፕቶከረንሲ ክፍያ መቀበሉ በማስረጃ ተረጋግጧል።

‎ተጠርጣሪው በጠላትነት የተፈረጀች ሀገርን በመርዳትና የኢራንን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በዛሬው ዕለት በስቅላት መቀጣቱን ዘገባው ጠቅሷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...