ማሊ ከ80 በላይ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዷን አስታወቀች

Date:

ማሊ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ ደርሼበታለሁ ያለቻቸዉን ከ80 በላይ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ወሰደች።

በወታደራዊ መንግስት የምትመራዋ ማሊ፤ በማዕከላዊና ምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ በፈጸመችዉ ጥቃት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላቸዉ ያለቻቸዉን ከ80 በላይ ታጣቂዎችን መግደሏን የጦር ኃይሏገልጿል፡፡

የጦር ኃይሉ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጠው  መግለጫ፤እርምጃዉ የተወሰደዉ በሰባት ከተሞች ላይ መሆኑን ገልጾ፤ በሴኔጋል ደግሞ ከሞሪታኒያ ጋር በሚዋሰኑበት ድንበር ጥቃቶቹ እንደተፈፀሙ ተናግረዋል፡፡

የታጣቂ ሀይሉ በበኩሉ በተቀናጀ መልኩ ጥቃት መፈፀሙን ገልጾ፤ሶስት የመንግስት ወታደራዊ ካምፖችን መቆጣጠሩን አስታዉቋል፡፡

የማሊ መንግስት በማሊ የተለያዩ አካባቢዎች ለ30 ቀናት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ  አዋጅ አዉጇል።

በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኒጀርን የያዘው የሳህል ቀጣና የዓለም የሽብር ማዕከል ነው ሲል ገልጾታል።

የሽብር ቡድኖቹም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በኮንትሮባንድ የጦር መሳሪያ ንግድ  ገቢያቸውን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደጉ ይገኛሉ ሲል አፍሪካኒውስ ዘግቧል።

ማሊ ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ በወታደራዊ ሃይል እየተመራች  መሆኑ ይታወቃል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...