ሜሪ ጆይ 50 ሺሕ ሕጻናትን ከችግር ለመታደግ አገር አቀፍ ጥሪ አቀረበ

Date:

ላለፉት 30 ዓመታት በበጎ አድራጎት ስራው የሚታወቀው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ፣ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለከፋ ችግር የተጋለጡ 50 ሺሕ ሕጻናትን ለመርዳት “የእኔም ልጆች ናቸው” በሚል መሪ ቃል መጠነ ሰፊ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ጀምሯል።

ይህ አገር አቀፍ ጥሪ በዋነኝነት ያተኮረው ከ7 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ዓላማውም ሕጻናቱ ከማህበረሰቡ ሳይነጠሉ የምግብ፣ የጤና እና የትምህርት ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ የነገ ተስፋቸውን ማለምለም ነው።

ይህንን ሰብአዊ ጥሪ የተቀበሉ ሴት ጋዜጠኞች፣ ደራሲያንና ምሁራን በራሳቸው አነሳሽነት ጥምረት በመፍጠር የንቅናቄው ግንባር ቀደም ተዋናይ ሆነዋል።

የጥምረቱ አባላት ከመቶ በላይ ሕጻናትን ስፖንሰር ለማድረግ ቃል በመግባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን፣ ወደ ተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች በመሄድ “እባካችሁ ‘የእኔም ልጆች ናቸው’ በማለት አግዙን” የሚል ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ። እስካሁንም ካነጋገሯቸው አካላት አበረታች ምላሽ እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።

ሜሪ ጆይ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ ሲተገብረው በቆየው “የቤተሰብ ስፖንሰርሽፕ” ፕሮግራም በርካታ ሕጻናትን ለከፍተኛ ትምህርትና ለራሳቸው የገቢ ምንጭ ማብቃት መቻሉን እንደ ትልቅ ልምድ ወስዶታል።

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅትም ይህንን የ50 ሺሕ ሕጻናት የድጋፍ ንቅናቄ ለማሳካት የለጋሽ ተቋማትና የኢትዮጵያውያን ደግነት እጅግ ወሳኝ መሆኑን በማሳሰብ፣ ሁሉም ዜጋ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...