Entrance tricks በዋናነት የተከፈተው እንዲሁ short አድርጎ ለማስተማር ብቻ ሳይሆን የማታውቋቸውን ሚስጥሮች እና ቴክኒኮች በተለይ የክፍል አስተማሪዎች የማይነግሯችሁን ነገሮች ለመንገር ነው ። ከዛሬ ነሀሴ 1 ጀምረን አንዳንድ ነገሮችን እንላችኋለን ።
🦋እቅድ አውጡ ;- ሙሉ ጊዚያችሁን ፃፉት ማሳካት የምትፈልጉትን የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅድ ብላችሁ ፃፋት ። ያወጣችሁትን እቅድ ምን ያህል እየተገበራችሁት እንደሆነ ክትትል አድርጉ ።
🦋የተጋነነ እቅድ አይኑራችሁ ;- ያለንበትን ሙድ ሁሌ ማስቀጠል ስለሚከብድ ቀለል አድርጋችሁ ጀምሩ።
🦋በቂ እንቅልፍ ተኙ ;- ከስምንት ያላነሰ 🤷♀️ ። ምሳሌ ከማታ 3-11 ወይም ከ 4-12 አዎ ተማሪ አይደላችሁ እንዴ
🦋እራሳችሁን ከጓደኞቻችሁ ጋር በፍጹም አታወዳድሩ ;- አስታውሳለሁ ሁላችንም ብዙ ጉረኛ 🙍♂️🙍 ጓደኞች አሉን ። ይመጡ እና እስካሁን የ አስራ አንደኛን cover አላደረክም እንዴ ይሉሀል ። cover እንደዚ ቀላል ነው እንዴ ትላለህ ። በቃ አለቀልኝ ትላለህ ።
🦋ሶሻል ሚዲያ መጠቀም አቁሙ (ቀንሱ) ;- social media ገዳይ ነው ። ጊዜን አዕምሮን ይገድላል ።በተለይ ቲክቶክ application እስካሁን ስልካችሁ ላይ ካለ uninstall አድርጉት ። 90% ጥላቻ እና ዘረኝነት ነው ይቅርባችሁ ። እመኑኝ
ከ negative ነገር ሁሉ ራቅ :- ጥቃቅን ነገሮችን ሁሉ ከሚያወሳስቡ ፤ እናልፍም ፤ አይሳካም ፤ common content ያደረጉት ሊጥሉን ስላሰቡ ነው ከሚሉ ጓደኞች ፤ በአንድ ሰአት እንዲገባችሁ አድርጎ ማስረዳት እየቻለ ዘጠኝ ሰአት ሙሉ ከሚንዛዛ አስተማሪ እንደዚያም ሆኖ ካልተረዳችሁት 🫣
🦋ጓደኛ ምረጥ ;- ስለጥናትህ ከሁሉ ጋር አታውራ ። የት እንደደረስክ ምን እንደቀረህ በጣም open mind የሆኑ ጓደኞችን መምከር የሚችሉ ንግግራቸው ያማረ አንዳንድ smart ሰዎች አሉ አደል እናንተ ትምህርት ቤት እነሱ ጋ ሂድና አማክራቸው …………ይቀጥላል ።
ጊዜው ገና ነው ቀድማችሁ መጀመራችሁ የሚሰጣችሁ ጥቅም ፤ አመቱን በሙሉ ጭንቀት እና መደናገጥ ሳይገጥማችሁ በ confidence ለማሳለፍ ነው ። ነሀሴ ላይ ጀምሮ በቀን 1 ስአት የሚያነብ ተማሪ መጋቢት ላይ ጀምሮ በቀን 5 ሰአት ከሚያነብ ተማሪ ይበልጣል ።
Entrance Tricks
