ሩሲያ ወደ ግብፅ የምትልከውን የስጋና የወተት ተዋጽኦዎች ለመጨመር ፍላጎት እንዳላት የሩሲያ የኢንዱስትሪና ንግድ ሚኒስትር ገለጹ፡፡
የሩሲያ ኩባንያዎች ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸውን የኢንተርኔት መሳሪያዎችን በስፋት እያቀረቡ ሲሆን፤ ይህም የሁለቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ትስስር እየተጠናከረ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም ሩሲያ የግብርና ምርቶችን ወደ ግብፅ ገበያ በስፋት የማስገባት ፍላጎት እንዳላት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሩሲያና ግብፅ በብሔራዊ ገንዘቦቻቸው በመገበያየት ንግዳቸውን ሊያጠናክሩ መሆኑን ስፑትኒክ በዘገባው አመልክቷል፡፡
