ኢትዮጵያ ከቡና የውጪ ንግድ በሀገሪቱ ታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ሰበሰበች

Date:

በበጀት ዓመቱ 10 ወራት በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ የቡና ኤክስፖርት አፈጻጸም መመዝገቡን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ሀገሪቱ በ10 ወራት ውስጥ ከቡና ብቻ ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ላይ ገቢ ማግኘቷንም የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 10 ወራት 354 ሺህ 302 ቶን ቡና ወደ ውጭ መላኩን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን የ145 ሺህ 316 ሺህ ቶን፣ በገቢ ደግሞ የ869 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ እንዳለው አስታውቀዋል፡፡

በ10 ወራት የኢትየጵያ ቡና ቀዳሚ መዳረሻ ሀገራትም በቅደም ተከተል ጀርመን፣ ሳዑዲ አረቢያ እናአሜሪካ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡

ለተመዘገበው ስኬት ከመንግስት ጋር በቅንጅት ርብርብ ላደረጉ አካላትም ዋና ዳይሬክተሩ ምስጋና ማቅረባቸውን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...