ሩስያ የራሷን ግድብ ማውደሟ ተሰማ

Date:

ሩስያ በዩክሬይን ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የራሷን ግድብ ማውደሟ ተሰማ። ሩስያ ግድቡን ያወደመችው የዩክሬይን ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን ለማገድ ነው ተብሏል። እጄን በእጄ ይሏል ይኼ ነው፡፡

የጀርመን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፤ ሩስያ ግድቡን የደረመሰችው ሦስት ቶን ይመዝናል በተባለ የጦር አውሮፕላን ቦምብ ሲሆን፤ ግድቡ ከዩክሬይን ድንበር በጥቂት መቶ ኪሎ ሜትሮች በምትገኘው ፖፖቭካ በተባለች መንደር አቅራቢያ ነው።

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፤ ዩክሬይን በቤልጎሮድ ዞን የማጥቃት እርምጃዋን እያጠናከረች ሲሆን፤ የዩክሬይን ጦር ግን በጉዳዩ ላይ እስከ አሁን ያለው ነገር የለም ተብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...