ሪከርዶቹ ፀድቀዋል

Date:

   

የዓለም አትሌቲክስ በዛሬው ዕለት ሰባት የአዋቂዎችና የአንድ ከ20 ዓመት በታች ሪከርዶችን ያፀደቀ ሲሆን አንዱ የኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

ትዕግስት አሰፋ ባለፈው ሚያዚያ 18 (April 27/2026) በተካሄደው የለንደን ማራቶን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በመግባት የሻምፒዮንነት ክብሯን ማስጠበቋ ይታወሳል።

ይህም እሷው እራሷ ኤፕሪል 27/2025 በለንደን አስመዝግባው የነበረውን በሴቶች ብቻ የተሮጠ የማራቶን የዓለም ሪከርድ (2:15:50) በ9 ሴኮንዶች ያሻሻለችበት ነው።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በመጨረሻዎቹ ማይሎች ከኬንያውያኑ ሔለን ኦቢሪ እና ጆይሲሊን ጄፕኮስጌይ ተነጥላ በመውጣት በድንቅ አጨራረስ ማሸነፍ ችላለች።

ኦቢሪ በ2:15:53 የግል ምርጥ ሰዓቷን በማስመዝገብ ሁለተኛ ስትወጣ፣ ጄፕኮስጌይ ደግሞ በ2:15:55 ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች። ይህም በአንድ የማራቶን ውድድር ሶስት ሴቶች ከ2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ በታች ሲገቡ በታሪክ የመጀመሪያው ሆኗል።

በሌላ በኩል በዛው የለንደን ማራቶን ኬንያዊው ሰባስቲያን ሳዌ 1 ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ በሆነ ድንቅ ሰዓት በማጠናቀቅ በተመሳሳይ አዲስ የዓለም ሪከርድ መያዙ ይታወሳል።

በዚህም የማራቶን ውድድርን ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት የመጀመሪያው ሰው ሆኗል። በዚህም የሀገሩ ልጅ የሆነው ኬልቪን ኪፕቱም ኦክቶበር 8/2023 በቺካጎ ማራቶን ይዞት የነበረውን የ2 ሰዓት ከ00 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ የዓለም ሪከርድ በ65 ሴኮንዶች ማሻሻል ችሏል።

ሳዌ ከኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጀልቻ እና ከኡጋንዳው ጃኮብ ኪፕሊሞ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርግ ቆይቶ፣ ውድድሩን ለማጠናቀቅ አንድ ማይል ሲቀረው ቀድሞ በመውጣት በ1:59:30 አሸንፏል።

ዮሚፍ ቀጀልቻም በ1:59:41 በማጠናቀቅ ከሁለት ሰዓት በታች መግባት የቻለ ሲሆን፣ ኪፕሊሞ ደግሞ በ2:00:28 ሶስተኛ ደረጃን አግኝቷል።

የሁለቱም ጀግና አትሌቶች የዓለም ሪከርድ በዛሬው ዕለት በይፋ መፅደቁን የዓለም አትሌቲክስ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

በምስጋናው ታደሰ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...