በአዲስ አበባ መርካቶ፣ በቅጠል ተራ አካባቢ የበጎነት መንደር በሚል ስያሜ ዘጠኝ የመኖሪያ ቤት ሕንፃዎች መገንባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
እንደ ከንቲባ ጽሕፈት ቤቱ መረጃ፣ ፕሮጀክቱ የዜጎችን የመኖሪያ ችግር ለመቅረፍ፣ የቤተሰቦችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና ማኅበራዊ ደህንነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።
የመኖሪያ ቤት ልማቱ የቤተሰቦችን የኑሮ ደህንነት ከማጠናከር ባለፈ፣ ለልጆች የተሻለ የኑሮ አካባቢ ለመፍጠርና የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት እንደሚያግዝ አስተዳደሩ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሮጀክቱ የከተማ ልማት ሥራዎችን ከዜጎች ፍላጎት ጋር በማጣመር የነዋሪዎችን ኑሮና አኗኗር ለማሻሻል እየሠራ ካለው ጥረት አካል መሆኑንም አመልክቷል።
