Home ዜና በመቐለ ቅርንጫፍ 402 ኩንታል ሰሊጥ በመረከብ አገልግሎቱን   ጀምሯል

በመቐለ ቅርንጫፍ 402 ኩንታል ሰሊጥ በመረከብ አገልግሎቱን   ጀምሯል

በመቐለ ቅርንጫፍ 402 ኩንታል ሰሊጥ በመረከብ አገልግሎቱን   ጀምሯል

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ 26ኛ ቅርንጫፉን በትግራይ  ክልል መቐለ ከተማ  በቅርቡ የከፈተ ሲኾን  ቅርንጫፉ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም 402 ኩንታል ሰሊጥ  በመረከብ ሙሉ በሙሉ ሥራውን ጀምሯል፡፡

የትግራይ ክልል ሰሊጥን ጨምሮ በርካታ ሰብሎች የሚመረቱበት አካባቢ በመሆኑ አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በዘመናዊ ግብይት ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲኾን ቅርንጫፉ አበክሮ ይሰራል፡፡
ቅርንጫፉ የተረከበው የመጀመሪያው ምርት ከሰሜን ምዕራብ ታሕታይ ቆራሮ ወረዳ የመጣ ሲኾን የምርቱ ባለቤትም  አቶ ሓጎስ መስፍን ናቸው፡፡

በክልሉ የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ አቅራቢዎችና ላኪዎች ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ በኾነው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በመገበያየት  ተጠቃሚ እንዲኾ አቶ ክብሮም ጸጋዬ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የመቐለ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪጅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በትግራይ ክልል መቐለ ቅርንጫፍ የተከፈተው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቅርንጫፍ  በክልሉ የሚገኙ አርሶ አደሮች ምርታቸውን ባሉበት አካባቢ ወደ ዘመናዊ ግብይት ሥርዓቱ ማቅረብ የሚችሉበትን ዕድል የሚያሰፋና  ረዥም ጉዞ፣ እንግልትና ከፍተኛ ወጪ የሚያስቀር ነው፡፡