በማይናማር ብሔራዊ የሀዘን ሳምንት ታወጀ

Date:

የሚንማር ገዢ ወታደራዊ መንግስት የአንድ ሳምንት ብሄራዊ ሀዘን ያወጀ ሲሆን በሀገሪቱ ከ1,700 በላይ ሰዎች በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መሞታቸው ታውቋል። ለሀዘኑ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ የሚውለበለብ ሲሆን ይህም እስከ እሁድ ኤፕሪል 6 ድረስ እንደሚቆይ የማይናማር ወታደራዊ መንግስት አስታውቋል። የምያንማር አመራር ሚን አንግ ኽላይንግ በየካቲት 2021 መፈንቅለ መንግስት ካደረጉ በኋላ በሀገሪቱ ስልጣን ላይ ይዘዋል። ወታደራዊው መንግስት የሲቪል መሪ የነበረችውን አንግ ሱንግ ኪን በማሰር በተቃዋሚዎች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል።

ከምያንማር መረጃ ለማግኘት ከባድ እንደሆነ የገለፀው እና በመሬት መንቀጥቀጡ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ማረጋገጥ አዳጋች ቢሆንም የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አርብ ዕለት እንዳስታወቀው “ከ10,000 በላይ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ጠቁሟል።”በምያንማር የሚገኙ ሆስፒታሎች በመሬት መንቀጥቀጡ ክፈኛ የተጎዱ ሲሆን በዚህም ላይ ሆስፒታሎች አደጋ በደረሰባቸው ሰዎች ተጨናንቀዋል ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባልደረባ ማርጋሬት ሃሪስ ተናግረዋል።

ቢያንስ ሦስት ሆስፒታሎች ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ ሲሆኑ ሌሎች 22 ቱ ደግሞ “በከፊል የተጎዱ እና በትክክል መሥራት የማይችሉ ናቸው” ። የተጎዱትን ከመከታተል በተጨማሪ የእርዳታ ሰራተኞች እንደ ኮሌራ ላሉ በሽታዎች መቋቋም አለባቸው ብለዋል። ሌላው ፈታኝ ሁኔታ፣ ከዚህ ቀደም ለተወሰኑ ክልሎች ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ከለከለው ከሚንማር ገዥው ወታደራዊ መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት የሻከረ መሆኑን ትናገራለች። “ሁልጊዜ ትግል ነበር የሚሉት ሃሪስ “ነገር ግን ይህ እንደገና የእኛ ሥራ ነው ፤ እነዚህን ነገሮች በመደራደር ስራ ማስጀመር” ሲሉ ተደምጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...