በረሀብ እና በአልሚ ምግብ እጥረት ምክንያት የሞቱ ተፈናቃዮች ቁጥር 992 መድረሱ ተነገረ

Date:

በትግራይ ክልል በሽሬ ከተማ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል በአልሚ ምግብ እጥረት እና በርሃብ ምክንያት የሞቱት ተፈናቃዮች ቁጥር 992 መድረሱን የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ጸሐዬ እምባዬ በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ የደረሰው ሰብአዊ ኪሳራ ተጠንቶ መጠናቀቁን እና ቁጥሩም ከ550 ወደ 992 ከፍ ማለቱን  ተናግረዋል። 

በአሁኑ ሰዓት በሽሬ ከተማ እና በአካባቢዋ ከ250 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ በርሃብና በሽታ እየተሰቃዩ መሆኑን አንስተው፤ የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በሽሬ ከተማ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በክልሉ የሚገኙት ተፈናቃዮቹ በ2015 ዓ.ም. ጥር ወር አካባቢ ጀምሮ የሚሰጣቸው ሰብአዊ እርዳታ በመቋረጡ ምክንያት፤ ተፈናቃዮች ለርሃብ እና ለበሽታ መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ለእያንዳንዱ ተፈናቃይ 15 ኪ.ግ. ዱቄት እርዳታ እንደሚሰጥ ቢያሳውቅም እየተሰጠ ያለው ግን 9 ኪ.ግ. መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ የሚላከው የእርዳታ እህል ከሚያስፈልገው ጋር ልዩነት አለው” ብለዋል።

በአጠቃላይ በትግራይ ክልል ከሱዳን የተመለሱ እና ወደ ቀያቸው ተመልሰው በጸጥታ ችግር ምክንያት IDP በተባለ ተቋም ሥር ያሉትን ሳይጨምር 970 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ መሆናውን ኃላፊው አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ተፅዕኖ ፈጣሪዎች” የተባሉ ግለሰቦች በምክክሩ እንዲሳተፉ በምን መስፈረት ተመረጡ?

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 17ኛ ቀን ውሎ የክልል ተወካዮች ጉባኤ...

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...

በፌደራሉ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በሚገኝ...

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...