በቃ !? ለዚሁ ነው ! ?አክቲቪስት ( ድምጻዊ ) ሰለሞን ተካልኝ በእርግጥም አረፈ

Date:

 በእውነታ ብቻ ሳይሆን በሀገር ባሕል ስለምመራ ( ባልመራ እንኳን አክብሮት ስላለኝ ) ባለቤቱ በሕይወት በሌላበት የመረረ ወቀሳ አላቀርብም ። " ምርጥ ነበረ "ም አልለውም ። " አክቲቪስት " ያልኩት በፊት የሚታወቅበትን ድምጻዊነት ትቶ በአክቲቪስትነቱ ስለገፋበት ነው ። በግሌ ሰው ከሞተ በኋላ መወቀስ የለበትም በሚለው አላምንም ። ጥላሁን ገሠሠ ሲሞት ሀገር ፍራሽ አውርዶ እንደተቀመጠለት ሁሉ ሁላችንም ስንሞት በየምንታወቅበት መንገድ መመስገንና መወቀስ አለብን ። ከሞትን በኋላ ተመልሰን የምናስተካክለው ነገር ስላለን አይደለም ። ድሮም ሕይወታችን ለሌላው መማሪያ ነው ።

     የሰለሞንን ሞት Zehabesha ላይ ሳነብ ደነገጥኩ እንጂ ደስ አላለኝም ። ወዲያው አዕምሮዬ ላይ የመጡት ቃላት " በቃ !? ለዚሁ ነው !? " የሚሉት ናቸው ። እስከዚህ ድረስ ነው የሰው ልጅ ሕይወት ። መቸም እንደ ሰለሞን ተካልኝ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ዥዋዥዌ የተጫወተ የለም ። የሰለሞን ነውር ከሕዝብ ጋር የገጠመው ብሽሽቅ ነው ። መረን የለቀቀው የአማራ ጥላቻው ነው ። ማንም የትግራይ ሰው ለፖለቲካው እንደ ኮንዶም ሊጠቀመው ካልሆነ " የእኔ " የሚለው አይመስለኝም ። አሁን የሰለሞን ቤተሰቦች ካሉ ሲሆን በነበረው የሚደሰቱ አይመስለኝም ። ለልጁ ምን ሰጠው ? ጥላቻ ።

    ይህን የምጽፈው ከአልጋ ሳልወርድ ነው ። እኔም ራሴ አሁን ከአልጋ ሳልወርድ ሞቼ ፣ ይሄ ያልጨረስኩት ጽሑፍ ተገኝቶ " ስለ ሰለሞን ተካልኝ የጀመረውን ጽሑፍ ሳይጨርስ ሞተ " ሊባልልኝ ይችላል ። የሕይወት ጉዳይ በዚህ ልክ እንዲሰማኝ ነው የምፈልገው ። የእኔ ሕይወት የሌሎች መማሪያ ነው ። አሁን ስለ ሰለሞን ስጽፍ የእኔ መኖር እየተሰማኝ አይደለም ። ተራነቴን ፣ ትንሽነቴን ፣ ኢምንትነቴን ይበልጥ እያስታወስኩ ነው ። እንዳልዘነጋው የምፈልገው የሕይወቴ ክፍል ሟችነቴ ነው ።  ትናንትም ዛሬም የሰለሞን አይነት ማንነት ያላችሁ ፣ ባለጊዜነት የሚሰማችሁ ፣ ቋሚ ሰውነት የሚያጓጓችሁ ፣ ከሕዝብ ጋር መበሻሸቅ ውስጥ ያላችሁ የማገናዘቢያ ልቦና ከሰጣችሁ ቆም ብላችሁ አስቡበት ። መቼም ቋሚነት አይሰማችሁ ። መኖር አያጓጓችሁ ። ምንም ቢሆን ከሕዝብ ጋር አትበሻሸቁ ። ሕዝብ ባይወዳችሁ እንኳን አይጥላችሁ ።

     እኔ በሰለሞን ተካልኝ ላይ እየፈረድኩ አይደለም ። ስለ እሱ እያሰብኩ ነው ። እሱ ነው እንዲህ የሆነው ። የሆነውን ነው የጻፍኩት ። ነገም በእኔ ላይ እንዲሁ ይባላል ። የሰለሞን ሕይወት ፣ ስቃዩ የሚያሳዝነኝ ዛሬ አይደለም ። በሕይወት እያለም ነው ደጋግሜ የጻፍኩት ። ሰለሞን ሕወሓትን መደገፉ አይደለም ችግሩ ፤ " ትግሬ ካልሆንኩ " ማለቱ ነው ። ሰለሞን በመሞቱ ተጠቀመ እንጂ አልተጎዳም ። ከሚጨንቅ ሕይወት ነው የተገላገለው ። ጥላቻ ስቃይ ነው ። ከዚያ ነው የተገላገለው ። የዳነው ። ስቃይ ነው የቀረለት በቃ ። እስከዚህ ድረስ ነው ።
ከቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...

በኢትዮጵያ በካንሰር ከሚያዙ ሕፃናት መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት ህክምና አያገኙም

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በካንሰር ከሚጠቁ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ...