በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

Date:

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5 በሬክተር መጠን የተመዘገቡት ሁለት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች መድረሳቸውን ተከትሎ ቢያንስ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል። ርዕደ መሬቱ በተለይም በዋና ከተማዋ ካራካስ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ከፍተኛ የነፍስ አድን ስራ እየተካሄደ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ የሚችል ነው ሲል አስጠንቋል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጡ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ከታዩት እጅግ ኃይለኛ ነው በማለት “ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ለሞት ዳርጓል” ብለዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ ማርኮ ሩቢዮ “የነፍስ አድን ቡድኖችን ፣ የህክምና ድጋፍ እና ሰብአዊ እርዳታን ወደ ቬንዙዌላ ዋሽንግተን እያሰማራች ነው” ብለዋል ።

ሩቢዮ በኤክስ ላይ ባጋሩት መልዕክት “ልባችን ዘመዶቻቸውን በሞት ካጡ ፣ ከተጎዱት እና ደፋር የነፍስ አድን ሰራተኞች ጋር ነው” ሲሉ አክለዋል።

የቬንዙዌላ ጊዜያዊ ፕሬዝደንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባስተላለፈችው መልዕክት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በማመስገን ከቬንዙዌላ ባለስልጣናት ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት ሲያደርጉ ነበር ብላለች። ፕሬዝዳንቷ በፌስቡክ ባሰራጨችው መግለጫ የአሜሪካ መንግስት ለቬንዙዌላ ድጋፍ እና አጋርነት መስጠቱን አክላለች ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...