
የኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 14ኛዉ የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርዒት የመዝጊያ እና የእውቅና መርሀ ግብር እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በኢሊሊ ሆቴል እሁድ መጋቢት 7 2017ዓ.ም ተካሄደዋል ።
በመርሀ ግብሩ ላይም ለአገር ውስጥና ለውጪ ተሳታፊዋች እውቅና የተሠጠ ሲሆን የንግድ ትርዒቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ላደረጉ በተጨማሪም የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተሳታፊዋች ሽልማት ተሰጥቷል ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ እንደገለፁት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዉስጥ የመሪነት ሚና የሚጫወት፣ ጠንካራና ዘላቂ አቅም ያለዉ አቅም እንዲፈጠር ብሎም ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የግሉ ዘርፍ ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው 14ኛው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ፤ የኢትዮጵያን ምርቶች፣ አገልግሎቶችና ግብዓቶች በማስተዋወቅ፣ ለአገራችን ኢንዱስትሪ ልማት እድገት፣ ለስራ ፈጠራ እና ለንግድ ስራ መስፋፋት የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች የቀረቡበት እንዲሁም የሀገር ዉስጥና የዉጭ ኩባንያዎች መካከል የገበያ ትስስር፣የእዉቀትና የልምድ ልዉዉጥ የተደረገበት ከመሆኑ አንጻር ውጤታማ ነበር፡፡
ከዚህም ባሻገር ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሆኑበት ይህ ኤግዚቢሽን ከውጭ የመጡ የንግድ አካላት የተሳተፉበት እንደመሆኑ ልምድ ለመለዋወጥ እና ትስስር ለመፍጠርም ትልቅ ጠቀሜታ ተገኚቶዋል ።
የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ እድሎችን የዳሰሰ የፖናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ የንግዱ ማኀበረሰብ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የተወከሉ የስራ ኃላፊዋች ተገኝተዋል።