በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አርሰናል ፣ ሪያል ማድሪድ እና ፒኤስጂ ወደ ሩብ ፍፃሜው አለፉ

Date:


በሜዳው ኤምሬትስ ባየር ሌቨርኩዘንን ያሰተናገደው አርሰናል 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል። በጨዋታው ድንቅ የነበሩት እንግሊዛዊያኑ ኤብሬቼ ኤዜ እና ዴክላን ራይስ ሁለት ውብ ጎሎችን ለመድፈኞቹ አስቆጥረዋል። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በድምሩ 3 ለ 1 በማሸነፍ የሩብ ፍፃሜው ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል። አርሰናል አሁን በሻምፒዮንስ ሊጉ በሚኬል አርቴታ አሠልጣኝነት ኤምሬትስ ላይ ካደረጋቸው 17 ጨዋታዎች 14ቱን በድል ተወጥቷል።

የውድድሩ ሀያል ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ሲቲ እና ፔፕ ጓርዲዮላን ዳግም ከውድድሩ አሰናብቷል። በኤቲሃድ በተደረገው ጨዋታ ሎስ ብላንኮዎቹ በቪኒ ጁኒየር ሁለት ጎሎች ታግዘው 2 ለ 1 ማሸነፍ ችለዋል። የማንችስተር ሲቲን የማስተዛዘኛ ግብ ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ ሲያስቆጥር በርናርዶ ሲልቫ በ 20ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ሪያል ማድሪድ በድምሩ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ማንችስተር ሲቲን ከውድድሩ ውጪ ሲያደርጉም ይሄ ባለፉት 5 አመታት ለ 4ተኛ ጊዜ ነው።

በሌላ ጨዋታ ቼልሲ በውድድሩ ሻምፒዮን ፓሪዛን ዤርሜ በድምሩ 8 ለ 2 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል። የዝውውር እገዳ በተጣለባቸው ማግስት ከውጤት ቅልበሳ ምኞት ጋር በስታምፎርድ ብሪጅ ፓሪዛዊያኑን የገጠሙት ሰማያዊዎች ትናንት ምሽትም 3 ለ 0 ተሸንፈዋል። ለፓሪሱ ክለብ ጎሎቹን ክቪቻ ክቫራስኬሊያ ፣ ብራድሊ ባርኮላ እና ሴኒ ማዩሉ አስቆጥረዋል።

በሌላ በኩል የአስደናቂው ቦዶ ግሊምት ጉዞ በስፖርቲንግ ሊዝበን ተገቷል። የኖርዌዩ ክለብ ትናንት ምሽት በስፖርቲንግ 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...