በአጎአ መታገድን 18 የውጭ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ለቀዉ ወጡ

Date:

የአፍሪካ የዕድገትና ዕድል ህግ (አጎአ) መታገዱን ተከትሎ ወደ 18 የሚጠጉ የውጭ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን ለቀው መውጣታቸው በአፍሪካ ዲቨለፕመንት ባንክ ግሩፕ (AfDB) ይፋ በተደረገ አዲስ ሪፖርት ተገለጸ። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የ45 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዲያጡ ምክንያት ሆኗል።

ባንኩ “Country Focus Report 2025 Ethiopia” በሚል ርዕስ ባወጣዉ ሰፊ የጥናት ግኝት መሰረት፣ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በአጎአ በኩል ለብዙ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አሜሪካ ገበያ የመግባት ዕድል ነበራት። ይሁን እንጂ በጥር 2022 የAGOA መታገድ ቀደም ሲል የተቋቋሙ የገበያ ትስስሮችን እና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን በእጅጉ ማቋረጡን ሪፖርቱ አስረድቷል።

ይህም ከኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚላኩ ምርቶች በ2023 በ24% እንዲቀንሱ አድርጓል። በተለይም በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ1,000 በላይ የሥራ ዕድሎች የተቋረጡ ሲሆን ለኢንዱስትሪ ፓርኮች በጠቅላላው 45 ሚሊዮን ዶላር የገቢ ኪሳራ አስከትሏል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...