የኢትዮጲያ አየር መንገድ እጅግ ዘመናዊ የአውሮፕላን ጥገና ወርክሾፕን ጨምሮ ፥ ዘመናዊ መጋዘንን አስመርቋል።
አየር መንገዱ ይህንን ዘመናዊ ልዩ ልዩ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከላት የተካተቱበትን ግዙፍ ማእከል ከ 150 ሚሊየን ዶላር በላይ በማውጣት ማስገንባቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በምረቃው ወቅት ተናግረዋል።
በ150 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች የአውሮፕላን ክፍሎች መጠገኛ፣ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል እና ከሰው ንከኪ ነፃ የሆነ መጋዘን ናቸው።
የጥገና ቁሳቁሶች የሚከማቹበት መጋዘኑ በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መሆኑ ተገልፃል።
የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥ እና የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ እና ሌሎች የተቋሙ እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ዲፕሎማቶች እንዲሁም በፕሮጀክቱ የተሳተፍ አካላት በምረቃው ወቅት ተገኝተዋል።
