በኢትዮጵያ ትልቁ የትምህርት ኤክስፖ ሊካሄድ ነው

Date:

አዲስ ቪዥን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ በኢትዮጵያ ትልቁን “አዲስ ቪዥን” የተሰኘ ሁሉን አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ 2025 ማዘጋጀቱን ገለጸ።

ኤክስፖው፤ ትምህርት ቤቶችንና ተማሪዎችን በሚያገለግሉ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የትምሀርት ተቋማትን፣ አቅራቢዎችን፣ አምራቾችንና አገልግሎት ሰጪዎችን አንድ ላይ በአንድ ቦታ እንደሚያገናኝ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል።

ተሳታፊዎች ከብዙ ባለድርሻ አካላት ጋር ለመገናኘት፣ አዳዲስ ምርቶችንና ቴክኖሎጂዎችን ለመተዋወቅ እንዲሁም አዳዲስ ትምህርታዊ መፍትሄዎችን በአንድ ማእከላዊ ቦታ የማግኘት እድል ይኖራቸዋል ተብሏል።

በዚህ የትምህርት ኤክስፖ የትምሀርት ተቋማት፣ የትምህርት ቁሳቁሶችን፣ ዩኒፎርሞችን፣ አልባሳትን፣ መጫወቻዎችንና የመጫወቻ ሜዳ አቅራቢዎች ምርታቸዉንና አገልግሎታቸዉን ያስተዋውቃሉ።

በሥርዓተ ትምህርት ልማት፣ በትምህርት ፈጠራና በሙያ መመሪያ ላይ የፓነል ውይይቶች ይደረጋል እንዲሁም ተማሪዎች፣ ወላጆችና  አስተማሪዎች የሚያወያዩባቸው  መድረኮች ይካሄዳሉ።

ኤክስፖው ከነሃሴ 22-24 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፣ ግዮን ሆቴል ይካሄዳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...