በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

Date:

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን የንግድ ልውውጥ ህጋዊ ለማድረግ እና ለማስተካከል የሚያስችል አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እና የኬንያ የጠረፍ ንግድ መመሪያ 1144/2018 ፣ በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በህጋዊ መንገድ እንዲያገኙ ለማስቻል እና ከሀገሪቱ ዋና የንግድ ማዕከላት ርቀው ለሚኖሩ ነዋሪዎች የሚፈጠረውን የምርት እጥረት ለመቅረፍ ያለመ ነው።

ሚኒስትሩ እንደገለፀዉ ፤ የመመሪያዉ ዋና ትኩረት አነስተኛ የድንበር ንግድን ማደራጀት እና መደበኛ ያልሆነውን የንግድ እንቅስቃሴ ወደ ህጋዊ ሥርዓት ማስገባት እንደሆነ አብራርቷል።

በዚህም መሰረት አዲስ የገንዘብ እና የጉዞ ገደቦች ተቀምጠዋል፤ አንደኛው ነጋዴው በወር የሚገበያይባቸው ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ ከ1,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም ወደ 155,000 ብር መብለጥ እንደሌለበት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ብቁ የሆኑ ነጋዴዎች በወር ከፍተኛው አራት ጊዜ ብቻ የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ማካሄድ እንደሚችሉ የሚደነግግ ነው።

“የድንበር አካባቢ” ተብሎ የተወሰነውም ከኢትዮጵያ በኩል 50 ኪሎ ሜትር እና ከኬንያ በኩል 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው ዞን ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ነው።

ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ለመሆን ነጋዴዎች በተጠቀሰው የድንበር አካባቢ በቋሚነት የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎች መሆን እና በአካባቢው አስተዳደር አካላት መመረጥ ይጠበቅባቸዋል።

ከአምስት ቀናት በፊት የፀደቀው መመሪያው ለንግድ እንቅስቃሴ የሚፈቀዱ 50 ዓይነት የዕቃ አይነቶች እንዳሉት በዝርዝር አስቀምጧል። ከእነዚህም መካከል ግብርና ምርቶች፣ ከብቶች፣ ጨርቃ ጨርቅ እና የቤት ውስጥ ንፅህና መጠበቂያዎች ይገኙበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...

ከቡና ኤክስፖርት 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ተገኘ

ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ኤክስፖርት 3 ቢሊየን የአሜሪካን...