በኢትዮጵያ 5 በመቶ የሚሆነው የወተት ምርት ብቻ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለሕዝቡ እንደሚቀርብ ተገለጸ

Date:


በኢትዮጵያ ለማኅበረሰቡ የሚቀርብ ብዙ መጠን ያለው የወተት ምርት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርብ 5 በመቶ ብቻ የሚሆነው የወተት አቅርቦት ጥራቱ የጠበቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ባለሥልጣን ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤት የእንሰሳት ተዋፅዖና አልሚ ምግቦች ኢንስፔክሽን ዴስክ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን፤ በሀገሪቱ አጠቃላይ የወተት ምርት አቅርቦት ላይ የጥራት ችግሮች መኖራቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል

ማንኛውም ሰው እንደፈለገ ወተት እያዞረ መሸጥ እንደማይችልና ይህ ግንዛቤ በማሕበረሰቡ ዘንድ እንደሌለ አለመኖሩን የገለጹት ኃላፊው፤ በተጨማሪም የወተት ምርትና ሽያጭ ከሚያስፈልገው ከፍተኛ ጥንቃቄ አንፃር በጀሪካንና በሌሎችም ባልተፈቀዱ ዕቃዎች ማጓጓዝ ጥራቱን ከማጓደል ባሻገር ለበሽታ አምጪ ተዋህስያን የሚያጋልጥ መሆኑን አስረድተዋል።

አክለውም፤ “ዘርፉ ያላደገ በመሆኑ የሚስተዋሉ የጥራት ችግሮችን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ አልተቻለም” ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በወተት ምርቶች በተለይም በባህላዊ መንገድ ለሕብረተሰቡ የሚቀርቡ ምርቶች ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚሹ በመሆናቸው፤ ወተት አቅራቢዎች በቂ ስልጠናዎችን በመውሰድ ዘመናዊ አካሄዶችን ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለዚህም በዋናነት ከሚስተዋሉ ችግሮች አንጻር የመኖ በበቂ ሁኔታ አለመቅረብ እና የእንሰሳት አያያዝ ተጠቃሽ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ ማለት ‘ሙሉ ለሙሉ ጥራት የጎደላቸዉ የወተት ምርቶች ገበያ ላይ አሉ’ ማለት እንዳልሆነ እና ጥራት ያላቸው የወተት ምርቶች ስለመኖራቸው አንስተዋል።

በባለሥልጣኑ በኩል የተጀመሩ የቁጥጥር ሥራዎችን በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎችም ተጠናክረው እንደሚሰሩም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

የዴስክ ኃላፊው አክለውም ባለሥልጣኑ የወተት ጥራትን ለማስጠበቅ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ሕጋዊ ሂደቱን በተመለከተ ለማሕበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...