በክረምት የሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል!

Date:

በሀገራችን አብዛኛውን ጊዜ በክረምት ወቅት አዘውትረው የሚከሰቱ በርካታ ተላላፊ በሽታዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ኮሌራና አተት በዋነኝነት የሚጠቀሱ በሽታዎች ናቸው፡፡ ከሰሞኑ በደቡብ ክልል በ42 ወረዳዎች የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን እና አራት ሺ ታማሚዎች መኖራቸውን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ የፌደራል መንግሥቱ እና ለጋሽ ድርጅቶች ለወረርሽኙ ፈጣን እና የተቀናጀ ምላሽ ለመስጠት እየሠሩ መኾኑንንም የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ወረርሽኙ በተከሰተባቸው አከባቢዎች ባለሙያዎች ማሠማራቱን የገለጸው ድርጅቱ ለማኅበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝም አመላክቷል። ወረርሽኙ በተከሰተባቸው አከባቢዎች የኮሌራ ማገገሚያ ማዕከላት መከፈታቸውንም የጠቆመው መግለጫው በማእከላቱ አስር እና ከዚያ በላይ ታማሚዎች በየቀኑ አገልግሎት እንደሚገኙ ገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅት ይህን ቢልም የኮሌራ ወረርሽኙ ደቡብ ክልል ላይ ብቻ ሳያበቀ ሰሞኑን በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ከ1000 በላይ የኮሌራ በሽታ ተጠቂዎች መገኘታቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህ የኾነው ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ለመግለጽ እንደሞከረው ወረርሽኙ በተከሰተባቸው አከባቢዎች አካባቢዎች ብቻ ሳይኾን ባልተከሰተባቸው ቦታዎች ጭምር ለማኅበረሰቡ በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ባለመሠራታቸው ወረርሽኙ በዚህ ልክ ሊስፋፋ ችሏል፡፡ አሁንም የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ርብርብ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት መግታት ያስፈልጋል፡፡ በተለይም ደግሞ ከኮሌራም በተጨማሪ የክረምት ወቅትን ጠብቀው የሚከሰቱ እንደአተትና ሳል የቀላቀሉ ጉንፋን መሰል በሽታዎች እንዳይከሰቱ በትኩረት መሥራት ይገባል፡፡ ለሕብረተሰቡ ሁልጊዜም ቢኾን በማስተማርና ግንዛቤ በመፍጠር ወረርሽኞቹ ከመከሰታቸው በፊት ማስቀረት ይገባል፡፡ በተለይም አሁን ላይ ሀገራችን በውስጥና በውጭ ተፈናቃዮች የተሞላች በመኾኗ እነዚህን መሰል የወረርሽኝ በሽታዎች በመጠለያ ጣቢያዎች ላይም እንዳይከሰቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡ የሚመለከተው አካልም በየዓመቱ ክረምት በገባ ቁጥር ይህ አይነት ችግር እንደሚከሰት አውቆ አስፈላጊውን ግንዛቤ ቀደም ብሎ በመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...