በወላይታ ሶዶ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

Date:

በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከሃዋሳ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ የሚጠራ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በተከሰተው አደጋም እስካሁን የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ አስተዳደር ዋና ሳጅን ዝናቡ ገዛኸኝ ተናግረዋል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አቅራቢያ በሚገኙ ጤና ተቋማት ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑን ዋና ሳጅን ዝናቡ ገልጸዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...