በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ የሰፈረው የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሥልጠና

Date:

ማይክሮሶፍት በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዙሪያ የሰጠው ኦንላይን ሥልጠና በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ125 ሺህ በላይ ሰዎችን በማስተናገድ ክብረ-ወሰን ይዟል።

ማይክሮሶፍት ይህን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የሰው ሠራሽ አስውሎት (AI) ክህሎት ሥልጠና ያዘጋጀው የዓለም አቀፍ ተጠቃሚዎቹን ትኩረት ለመሳብ ነበር፡፡

በዚህም ተሳክቶለት ኮርሱ በአዝናኝነቱ እና ሳቢነቱ በአጭር ጊዜ በርካታ ሰልጣኞችን በማስተናገድ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰፍሯል፡፡

ሥልጠናው በቴክኖሎጂ እና ንግድ ዘርፍ ለቀጣዩ ትውልድ ልዩ ተነሳሽነትን ለመፍጠር ያለመው የ50 ቀናት ዘመቻ አካል ነው።

የዕለት ተዕለት ተግባራትን ቀላል ማድረግ፣ ውጤታማ የሆኑ ዕቀዶችን ማዘጋጀት፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎችን መፍጠር፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ‘ቻት’ መተግበሪያዎችን ማዘጋጀት እና መረጃዎን ለማረጋገጥ ሰው ሠራሽ አስተውሎትን መጠቀም የመሳሰሉ ክህሎቶች በሥልጠናው ተካትተዋል።

ሠልጣኞች ኮርሱን ሲያጠናቅቁ የመውጫ ጥያቄዎችን የሚጠየቁ ሲሆን፣ ማይክሮሶፍትም ብቁ መሆናቸውን ሲያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል።

በዚህም በ24 ሰዓታት ወስጥ 126 ሺህ 151 ሰዎች ሥልጠናውን በትክክል ማጠናቀቃቸው ማረጋገጡን የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ አስታውቋል፡፡

የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ባጋራው መረጃ ማይክሮሶፍት በሰው ሠራሽ አስተውሎት ክህሎት ሥልጠና በአንድ ቀን በርካታ ተሳታፊዎችን በማስተናገድ ክብረ-ወሰን መያዙን ጠቅሶ፣ የምሥክር ወረቀት እንዳበረከተለት ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሺ ጂምፒንግ ምርጥ መሪ ነው!”- ትራምፕ

አሜሪካና ቻይና ተፎካካሪ ሳይሆኑ አጋርነት ያላቸው ሀገራት ናቸው አሉ...

የአሜሪካ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች በኢትዮጵያ ላይ የንግድ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ

በአሜሪካ የሚገኙ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች፣ የቻይና ኩባንያዎች የአሜሪካን...

ምርጫ ለሰላም ግንባታ

ግዮን መጽሔት :-ለኢትዮጵያ ሰላም ምርጫ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።...