Home ዜና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአራት ቀናት ከ230 በላይ እንስሳት መሞታቸው ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአራት ቀናት ከ230 በላይ እንስሳት መሞታቸው ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል  በአራት ቀናት ከ230 በላይ እንስሳት መሞታቸው ተገለጸ


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ኡባ ደብረጸሐይ እና ዛላሕ ወረዳዎች እንዲሁም በሻውላ ከተማ አስተዳደር ከመጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ በተከሰተ የእንስሳት ወረርሽኝ በርካታ ቁጥር ያላቸው እንስሳት መመታቸው ተገለጸ።

የበኡባ ደብረጸሐይ ወረዳ ብቻ ባለፉት አራት ቀናት ከ238 የሚሆኑ እንስሳት መሞታቸውን አርብቶ አደሮች እና የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች አስታውቀዋል።

የኡባ ደብረጸሐይ ወረዳ የግብርና ጽሕፈት ቤት ሐላፊ የሆኑት አቶ አይሬ ሞርጫ ስለመንሰኤው እስከአሁን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም “አየሩ ጸሐያማ ሆኖ ነው የከረመው ከዛ ግን ከሰሞኑ የተወሰነ ዝናብ መጣል ጀምሮ ነበረ” ሲሉ የወረርሽኙም መነሻ ከዚሁ የአየር መቀየር ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል።