በጊኒ የፖለቲካ ፓርቲዎች መፍረስ

Date:

በጊኒ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዙት የመማዲ ዱምቡያ ወታደራዊ መንግሥት፣ በሌሊት ባወጣው አዲስ አዋጅ ሦስት ዋና ዋና ተቃዋሚዎችን ጨምሮ 40 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማፍረሱን አስታወቀ።

የግዛት አስተዳደር ሚኒስቴር ውሳኔውን ያስተላለፈው ፓርቲዎቹ “ግዴታቸውን አልተወጡም” በሚል ምክንያት ሲሆን፣ አዋጁ የፓርቲዎቹን ምልክቶች መጠቀም የሚከለክልና ንብረቶቻቸውንም በቁጥጥር ሥር የሚያውል ነው።

ከፈረሱት መካከል በስደት የሚገኙት የሴሉ ዳሌይን ዲያሎ (UFDG) እና የቀድሞው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ (RPG) ፓርቲዎች ይገኙበታል።

እ.ኤ.አ. ከ2021 ጀምሮ አገሪቱን በጠንካራ እጅ እየመሩ ያሉት ዱምቡያ፣ ተቃውሞዎችን በማገድና መሪዎችን በማሰር እንዲሁም በማሳደድ ይወቀሳሉ።

የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪል ማኅበራት ድርጊቱን “አምባገነናዊ” በማለት የኮነኑት ሲሆን፣ እንደ ዑመር ሲላ እና ማማዱ ቢሎ ባህ ያሉ ታዋቂ አክቲቪስቶች ከሐምሌ 2024 ጀምሮ በግዳጅ መሰወራቸው በጊኒ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።

ይህ እርምጃ በሀገሪቱ ያለውን የዴሞክራሲ ተስፋ ይበልጥ ያጨለመ እንደሆነ ተነግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...