በጋምቤላ ከተማ ሌሊቱን በጣለው ከባድ ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል ። በተለይ በ05 ቀበሌ አንዳንድ አካባቢ የግለሰቦች መኖሪያ ቤት ውስጥ በመግባት በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የእግረኛ እና የመኪና መንገዶች ላይም ውሃ ስለተኛባቸው ለመተላለፍ አስቸጋሪ አድርጎታል ።
የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ሳይመን ሙን ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከክረምት ዝናብ ጋር ተያይዞ በሰውና ንብረት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የጎርፍ መፋሰሻ ቱቦዎችን በመክፈት የውሃ ፍሰትን መቆጣጠር እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የክረምት ወራት ገና ከመሆኑ የተነሳ የዝናብ መጠን ሊጨምር ስለሚችል የከተማችን ነዋሪዎች ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ጨምረው ገልጸዋል።
