በጋዛ የሃማስ መሪ የሆነው መሀመድ ሲንዋር መገደሉን እስራኤል አስታወቀች

Date:

የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፥ በእስራኤል በጥብቅ ከሚፈለጉት የሃማስ ሰዎች መካከል አንዱ እና በጋዛ የሃማስ መሪ የሆነው መሃመድ ሲንዋር በጦራቸውመገደሉን ገልጸዋል።

መሀመድ ሲንዋር ባሳለፍነው ግንቦት 5  ቀን በደቡባዊ ካን ዮኒስ የአውሮፓ ሆስፒታል ግቢ እና አካባቢ ላይ የተደረገው የእስራኤል ከፍተኛ ጥቃት ዒላማ መሆኑ ተገልጿል። የእስራኤል ወታደራዊ ሃይል የሃማስን የምድር ውስጥ የጉዞ መስመር እና የተለያዩ ቢሮዎች በጥቃቱ ማውደም እንደቻለ በወቅቱ ገልጾ ነበር።

በጋዛ ሃማስ የሚመራ የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ በጥቃቱ 28 ሰዎች መሞታቸውን ቢገልጽም ከሲንዋርን ጋር በተያያዘ በህወት ይኑር ወይም ይሙት ምንም አይነት መረጃን አላወጣም።

እ.ኤ.አ ጥቅምት 7/ 2023 በእስራኤል ላይ የተፈፀመው ጥቃት ዋና አቀነባባሪ የተባለው እና የመሀመድ ሲንዋር ወንድም የሆነው ያህያ ሲንዋር ባለፈው ጥቅምት ወር በእስራኤል ወታደሮች መገደሉ ይታወሳል ሲል የዘገብው ቢቢሲ ነው።

የእስራኤል እና ሃማስ ግጭት ለ20 ወራት የዘለቀ ሲሆን፤ በተለያየ ጊዜ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ቢደረጉም እስካሁን ዘላቂ መፍትሄ ሊበጅለት አልቻለም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...