Home ዜና ባለፈው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተከሰተው የትራፊክ አደጋ 45 በመቶው አምራች የኅብረተሰብ ክፍል ላይ መሆኑ ተገለጸ

ባለፈው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተከሰተው የትራፊክ አደጋ 45 በመቶው አምራች የኅብረተሰብ ክፍል ላይ መሆኑ ተገለጸ

ባለፈው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተከሰተው የትራፊክ አደጋ 45 በመቶው አምራች የኅብረተሰብ ክፍል ላይ መሆኑ ተገለጸ

በ2016 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተከሰተው የትራፊክ አደጋ 45 በመቶው አምራች የኅብረተሰብ ክፍል ላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባልሥልጣን ገለጸ፡፡
ባለሥልጣኑ ይኼን የገለጸው ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሌሎች አጋር ተቋም ጋር በጋራ በመተባበር በከተማ አቀፍ ደረጃ ለ9ኛ ጊዜ የፖሊስ መረጃን በመጠቀም ያዘጋጀውን ዓመታዊ የመንገድ ደኅንነት ሪፖርት ይፋ ባደረገው መግለጫ ነው፡፡   
የከተማዋን ወቅታዊ የመንገድ ደኅንነት በሰፊው ዳሷል በተባለው በዚህ ሪፖርት መሠረት፣ በመዲናይቱ በ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት 401 ሰዎች በመንገድ ትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከ2015 ዓ.ም. አንፃር በሰባት ሰዎች መቀነሱ ተነግሯል። የከባድ አደጋ ጉዳት መጠን ሦስት በመቶ መቀነሱ ተገልጿል። 45 በመቶ የሞት አደጋ የተመዘገበው አምራች የኅበረተሰብ ክፍል በሆኑት ከ20 እስከ 39 ዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዜጎች ላይ ነው ተብ…

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140231/